ወሎ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በሶስቱም ግቢ ከሁለተኛ አመት በላይ ያሉ ነባር መደበኛ ተማሪዎችን ዛሬ ማለትም በ08/01/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተቀበለ ነው።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ቢንያም ሽመልስ አቀባበሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ከሁለተኛ አመት በላይ ያሉ ነባር ተማሪዎችን ከ08_09/01/2018 ዓ.ም ለመቀበል በተደረገው ጥሪ መሰረት በዛሬው እለት በሶስቱም ግቢዎች የተማሪዎች አቀባበል እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት እስከ ነገ 0901/2018 ዓ.ም ድረስ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ 4876 በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ 1646 እና በልዕለ ህክምና ግቢ 1492 ተማሪዎች በአጠቃላይ 8014 ተማሪዎች ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል።

ትምህርት መስከረም 15 የሚጀምር መሆኑንና ለዚህም ተገቢውን ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል ።

የተማሪዎች አግልግሎት ዲን ዶ/ር ብርሃኑ ግርማ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው ባደረገው ጥሪ መሰረት ተማሪዎች ወደ ግቢ እየመጡ መሆኑንና ቅበላው በበይነመረብ /online/ በመሆኑ ያለምንም ችግር በሰላማዊ መንገድ እየተስተናገዱ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ዶ/ር ብርሃን አያይዘውም በተማሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት በኩል ተማሪዎችን ከመቀበል ባለፈ ትምህርታቸው ላይ በማተኮር ውጤታማ መሆን እንዲችሉ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸው ሁሉም ተማሪዎች መግባታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የስብዕና ግንባታ ስልጠና ለመስጠት መታቀዱንም ጠቁመዋል።

Scroll to Top