በወሎ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው የፕሮጀክት አስተዳደር ስልጠና ተጠናቀቀ

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ5 ቀናት ሲሰጥ የነበረው ልምዶችን ማጋራት ላይ መሰረት ያደርገ የፕሮጀክት አስተዳደር ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስልጠናው በዩኒቨርሲቲው ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በማዕድንና ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በጋራ የተዘጋጀ ነው። አላማውም በዋናነት እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተሻለ ጥራትና ፍጥነት ለመተግበር የሚረዱ እውቀትና ልምዶችን ችግር ፈቺ በሆነ መልኩ ለመማማር እንዲሁም ተቋማዊ አቅም ለማጎልበት ታስቦ የተሰጠ መሆኑን የኮ/ቴ/ኢ/ አካዳሚክ

ጉዳዮች ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አለሙ ጆርጊ በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል።

በዘርፉ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በመምራት ሰፊ እውቀትና ልምድ ባካበቱ ተጋባዥ እንግዶች ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው በሶስቱም ካምፓሶች ያሉ የምርምር ጽ/ቤቶች፣ የግዥና ፋይናስ ኃላፊዎች፣ በሁለቱም ተቋምት የጋራ ፕሮጀክት ስራዎችን የሚመሩ ኃላፊዎች እና ከአጋር ድርጅቶች የተጋበዙ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ፕሮግራሙን በማጠቃለያ ንግግር የዘጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀዋ ወሌ ስልጠናውን ላዘጋጁት እና ለተሳታፊዎች ምስጋና በማቅረብ እንዲህ አይነት ስልጠናዎች የፕሮጀክት ስራዎችን በትብብር ለመስራት ትልቅ አቅም ይፈጥራሉ ብለዋል።

Scroll to Top